Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፖላንድ ሳዑዲ ዓረቢያን 2 ለ 0 አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ በምድብ ሶስት የሚገኙት ፖላንድ እና ሳዑዲ ዓረቢያ የሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
በዚህም ፖላንድ ሳዑዲ ዓረቢያን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነጥቧን ወደ አራት ከፍ ማድረግ ችላለች፡፡
በተቃራኒው በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ጥሩ ተንቀሳቅሳ አርጀንቲናን ያሸነፈችው ሳዑዲ በነበረችበት ሶስት ነጥብ ላይ ተገትታለች፡፡
ሳዑዲ ዓረቢያ በመጀመሪያ አጋማሽ ያገኘችውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳትጠቀምበት ቀርታለች፡፡
Exit mobile version