አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከፈረንጆቹ ሕዳር 15 ጀምሮ 2 ሺህ 400 ሜትሪክ ቶን ምግብ እና 100 ሺህ ሊትር ነዳጅ ትግራይ ማድረሱን ገለጸ፡፡
250 ቶን የሕክምና መሣሪያዎችን በሎጅስቲክሱ በኩል ወደ ክልሉ ማጓጓዙንም ነው ጨምሮ የጠቆመው፡፡
በዓለም የምግብ ፕሮግራም መሪነት የተመድ የዓየር የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት አገልግሎቱም ከዛሬ ጀምሮ ወደ መቐለ በረራ መጀመሩንም ነው በገጹ ባሰፈረው መረጃ ያስታወቀው፡፡