አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጥታ የሚፈጸምን የትኬት ሽያጭ ማቆሙን አስታወቀ።
አየር መንገዱ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ለየትኛውም ጉዞ የሚፈጸምን የትኬት ሽያጭ በኢንተርኔት አማካኝነት እንደሚሰጥ አስታውቋል።
እርምጃው እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በማለም የተወሰደ መሆኑንም ገልጿል።
በዚህም የትኬት መሸጫ ቢሮዎች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለጊዜው ይዘጋሉ ነው ያለው።
ደንበኞችም አገልግሎቱን አየር መንገዱ ባዘጋጃቸው የሞባይል መተግበሪያዎችና በባንኮች ማግኘት እንደሚችሉም ነው የገለጸው።