Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም ከቴሌ ብር ጋር የተሳሰር የመገበያያ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ከሲኔት ሶፍትዌር ቴክኖሎጅስ ጋር በመተባበር ማህበረሰቡን በቀላሉ መገበያየት የሚያስችል ከቴሌ ብር ጋር የተሳሰር የመገበያያ ተሞክሮ ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል፡፡

ይፋ የተደረገው አዲሱ የቴክኖሎጂ አሰራር ፈጣን እና አስተማማኝ በሆነ መልኩ የሻጭ እና ገዢን ጊዜ መቆጠብ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በዚህም ሀገሪቷ ላይ ያለውን የገንዘብ ዝውውር በማሳለጥ የግብይት ሒደቱን በአስተማማኝ መሰረት ላይ መመስረት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

ኢቲዮ ቴሌኮም በየጊዜው አዳዲስ አሰራሮችን እያስተዋወቀ እና አመርቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ሒደቱን አጠናክሮ መቀጠሉም በመርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

Exit mobile version