ስፓርት

ስፔን ኮስታሪካን ከግማሽ ደርዘን ጎል በላይ በማስቆጠር አሸነፈች

By Alemayehu Geremew

November 23, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው አራተኛ ቀን ውሎ ስፔን ከግማሽ ደርዘን ጎል በላይ በማስቆጠር አሸንፋለች።

በምድብ 5 የተደለደለችው ስፔን የደቡብ አሜሪካዋን ኮስታሪካን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችላለች።

ዳኒ ኦልሞ፣ ማርኮ አሴንሲዮ፣ ጋቪ፣ ካርሎስ ሶለር እና አልቫሮ ሞራታ አንድ አንድ ጎሎችን ሲያስቆጥሩ ፌራን ቶሬስ ሁለት ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።

በምድቡ ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን ባልተጠበቀ ሁኔታ 2 ለ 1 መሸነፏ ይታወሳል።