የሀገር ውስጥ ዜና

ሰሎሞን አረዳ በተመድ የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው መሾም ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ውክልናን ያስገኘ መሆኑ ተመለከተ

By Alemayehu Geremew

November 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የውስጥ ፍትሕ ሥርዓት ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው ለተሾሙት ሰሎሞን አረዳ የአሸኛኘት ሥነ ስርዓት አካሄደ፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው÷ አጋጣሚው ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም በአጠቃላይ የሚወክል ነው ተብሏል፡፡

በመንግሥታቱ ድርጅት መሰል አጋጣሚዎች አነስተኛ መሆናቸውን ጠቁመው፥ ዕድሉን በመጠቀም ግለሰቡ የኢትዮጵያን የሕግ ፍላጎት እንደሚያንጸባርቁ እምነት እንደተጣለባቸው የሥራ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል፡፡

በምስክር ተሥፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-