Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አርጀንቲና ባልተጠበቀችው ሳዑዲ የዓለም ዋንጫውን በሽንፈት ጀምራዋለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ሶስተኛ ቀን ውሎ ሳዑዲ ዓረቢያ ያልተጠበቀ ድል አስመዝግባለች።

ከደቡብ አሜሪካዋ አርጀንቲና ጋር የተጫወተችው ሳዑዲ ከመመራት ተነስታ 2 ለ 1 አሸንፋለች።

በጨዋታው ሊዮኔል መሲ በ10ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠረው ጎል አርጀንቲና 1 ለ 0 መምራት ብትችልም ሳዑዲዎች በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታውን ውጤት ቀይረውታል።

አል ሼሪ እና አል ዳውሳሪ በአሰልጣኝ ሄርቬ ሬናርድ ለምትመራው ሳዑዲ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

አሰልጣኝ ሄርቬ ሬናርድ ከዚህ ቀደም ዛምቢያን እና አይቮሪኮስትን በመያዝ የአፍሪካ ዋንጫን ማሸነፍ ችለዋል።

በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ቀን ውሎም ለዋንጫው ግምት ካገኙ ሀገራት መካከል አንደኛዋ የሆነችውን አርጀንቲናን በማሸነፍ ያልተጠበቀውን አሳክተዋል።

 

 

Exit mobile version