Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአለም ዋንጫ ሴኔጋል በኔዘርላንድስ ተሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው ቀን የኳታር የዓለም ዋንጫ ጨዋታ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 ተሸንፋለች፡፡

የኔዘርላንድስን የማሸነፊያ ጎሎች የፒኤስቪው አጥቂ ኮዲ ባክፖ እና የአያክሱ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ዴቪ ኬላሰን አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው የተሳኩ ሙከራዎችን ማድረግ የቻለችው ሴኔጋል ኔዘርላንድስን መፈተን ብትችልም በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠረባት ጎል ተሸንፋለች፡፡

የአጥቂያቸው ሳዲዮ ማኔ በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጭ መሆን ደግሞ ለሴኔጋል አጥቂ ክፍል መሳሳት ግልፅ ምክንያት ሆኖ ታይቷል፡፡

Exit mobile version