አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዳር 12 ወይም “ህዳር ሲታጠንን” ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
ህዳርን በፅዳት በሚል መሪ ቃል ነው የፅዳት ዘመቻው የተካሄደው።
ጃክሮስ አካባቢ የተካሄደው የፅዳት ዘመቻ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር ነው የተካሄደው።
በፅዳት ዘመቻው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን እና በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ የአስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ከንቲባዋ በመልእክታቸውም የከተሜነት መለኪያው ከተማን ፅዱ፣ ውብና አረንጓዴ ማድረግ በመሆኑ አዲስ አበባን ውብ፣ ፅዱ እና ለኑሮ አመቺ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
አካባቢን ስናፀዳ ከከፋፋይ ሀሳቦችም በመራቅ መሆን አለበት ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።
በፍቅርተ ከበደ