አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 22ኛው የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት በድምቀት ተካሂዷል፡፡
የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ የተካሔደው በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታ እያስተናገደ በሚገኘው እና 60 ሺህ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው አል ባይት እስታዲየም ነው፡፡
በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ የውድድሩ ሳውንድ ትራክ ተብሎ በፊፋ ዕውቅና የተሰጠው “ሃያ ሃያ” (አብሮነት ይሻላል) የሚለው ቀርቧል፡፡
አስተናጋጇ ኳታር ከደቡብ አሜሪካዋ ኢኳዶር ጋር የመክፈቻ ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው፡፡
ኳታር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 18 ቀን 2022 ድረስ ለምታስተናግደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ስምንት ስታዲየሞች መርሐግብሮቻቸውን ለማከናወን ተሰናድተዋል፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!