አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚፈፀም ስርቆት እና ማጭበርበርን ለመከላከል የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “ውስን ሀብታችን የሆነውን መሬት መዝግበን ለመያዝ የጀመርነውን የካዳስተር ሥራ ምን ላይ እንዳለ ገምግመናል” ብለዋል።
አክለውም፥ ችግሮችን ፈትተን የተሟላ ሥራ ለመሥራት በመሬት ዘርፍ የሚፈፀመውን ማጭበርበርና ሌብነት ለመከላከል የጀመርናቸውን ሥራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከ10 ዓመት በፊት ጀምሮ ሕጋዊ የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ (ካዳስተር) ሥራ እየሠራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ባለፈው በጀት ዓመት ሚያዚያ ወር ድረስ ባለው መረጃ መሠረት÷ በመዲናዋ የለሚኩራ ክፍለ ከተማን ሳይጨምር በ10 ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ 25 ቀጠናዎች ላይ የመሬት ይዞታን የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራ ተሰርቷል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከ2008 እስከ 2011ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ከ118 ሺህ በላይ የመሬት ይዞታዎችን እና ከ161 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በካዳስተር መመዝገብ ችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!