Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በ8ኛ ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

በዚህም 10 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የአርባምንጭ ከተማን ግብ አሸናፊ ኤልያስ ሲያስቆጥር የፋሲል ከነማን ግብ ደግሞ ፍቃዱ ዓለሙ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 1ሰዓት ለገጣፎ ለገዳዲ ከወልቂጤ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በወልቂጤ ከተማ 3 ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የወልቂጤ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ጌታነህ ከበደ(ሁለቱን ግቦች ) እና የኋላሸት ሰለሞን አስቆጥረዋል፡፡

Exit mobile version