የሀገር ውስጥ ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመካከለኛና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሥልጠና እየሰጠ ነው

By Melaku Gedif

November 19, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመካከለኛና ከፍተኛ የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች በውጭ ግንኙነትና በብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው።

 

ስልጠናው በአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል ነው እየተሰጠ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

 

በሥልጠናው የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር፣ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚጋፋ የሌላውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መመከት የሚያስችል ግንዛቤ እየተሰጠ ነው።

 

ሥልጠናውን እየሰጡ ያሉ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፥ ኢትዮጵያውያን አንድትን ከፋፋይ አስተሳሰብ ራሳቸውን ማላቀቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

 

አያይዘውም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እንደ በለጸጉት ሀገራት ሃያል ባትሆንም በሃያላን ውሳኔ በሚመራ ዓለም ውስጥ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ሚናዋን በውል ማሳየት ያስፈልጋል ብለዋል።