የሀገር ውስጥ ዜና

የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ጉዞ ጀመሩ

By ዮሐንስ ደርበው

November 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪነት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ጀምረዋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል በኩል ለትግራይ ክልል ህዝብ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህ መሠረትም ሁለት የነዳጅ ቦቴዎችን ጨምሮ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች ዛሬ በአፋር ኮሪደር በኩል ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡

የአፋር ሕዝብና መንግስት ለወንድም የትግራይ ሕዝብ የሰብዓዊ እርዳታው እንዲደርስ ካሁን በፊት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!