Made with LogoLicious Add Your Logo App

የሀገር ውስጥ ዜና

ጫናዎችን የምንቋቋመው አንድነታችንን ስናጠናክር ነው- ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

By ዮሐንስ ደርበው

November 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጫናዎችን የምንቋቋመው ውስጣዊ አንድነታችንን ስናጠናክር መሆኑን በተግባር አሳይተናል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ያለመ የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ዶክተር ይልቃል በመድረኩላይ ባደረጉት ንግግር የአማራ ሕዝብ ከውስጥና ከውጭ በተሰነዘሩ ሴራዎች ያንዣበቡበት ፈተናዎች በሕዝቡ አንድነት ከሽፈዋል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በጠንካራ ሥራ ያመጣነውን ሰላም አጠናክረን በመቀጠል የሕዝባችንን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት መሥራት አለብን ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

አማራና ቅማንት አንድ መዓድ የሚቋደሱ፤ በማህበራዊ ትስስር የተቃኙ ሁነው ሳለ ወደ ግጭት እንዲገቡ የተደረገበት ሴራ ብዙ ዋጋ አስከፍሎን ቆይቷል ብለዋል፡፡

የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሰላም አማካሪ ምክር ቤት ተቋቁሞ ሰፊ ጥረት ተደርጎ አሁን ላይ ለደረስንበት ሰላም አድርሶናል ማታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ሲመለሱ ያሳዩት ፍቅርና መተሳሰብ በአንድነት ከመኖር ውጭ ሌላ ምርጫ እንደሌለ በተግባር አሳይቶናል ነው ያሉት፡፡

ሰላም በማጣታችን ብዙ ተጎድተናል፣ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል፣ ከዚህ ተምረን ለሰላም ዘብ በመቆም ውስጣዊ አንድነታችንን አጠናክረን የጠላትን ዓላማ ማክሸፍ ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!