Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወ/ሮ ዳግማዊት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከክልል የትራንስፖርት ዘርፍ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 17፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከክልል የትራንስፖርት ዘርፍ አካላት ጋር ተወያይተዋል።

ከሁሉም ክልል የትራንስፖርት ዘርፍ ተቋማት ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ በተካሄደው በዚህ ውይይት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል ።

ከዚህ ባለፈም የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት መደረጉን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በውይይቱ እስካሁን በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት በክልሎች በጅምር ደረጃ የሚታየው እንቅስቃሴ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የተጀመረው ሥራ በፍጥነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ መቀመጡም ተመላክቷል።

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version