Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ በአቦት ወርልድ ማራቶን ደረጃ በሴቶች ቀዳሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ በአቦት ወርልድ ማራቶን ሜጀርስ የደረጃ አወጣጥ መሰረት በሴቶች ቀዳሚ ሆናለች፡፡

ደረጃው የወጣው በ6 ዋና ዋና የማራቶን ውድድር ማለትም በበርሊን፣ በለንደን፣ በቦስተን፣ በቶኪዮ፣ በቺካጎ እና በኒውዮርክ የማራቶን ውድድር ውጤት መሰረት ሲሆን አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ የውድድር አመቱ ምርጥ አትሌት ሆናለች፡፡

የውድድር ዘመኑን በበላይነት ማጠናቀቋን ተከትሎ አትሌቷ የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆኗንም ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ የኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የማራቶን አሸናፊ ስትሆን በኒውዮርክ ማራቶን ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

በወንዶቹ የአቦት ወርልድ ማራቶን ሜጀርስ የደረጃ አወጣጥ ደግሞ የማራቶን ንጉሱ ኬኒያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ማሸነፉን ከወርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version