Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እያደረኩ ነው – የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ስንዴ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ከላኪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ገለጸ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፥ ኢትዮጵያ የእርዳታ ስንዴ ከማስገባት አልፋ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ስንዴ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወደ ውጭ የሚላከው ስንዴ ከሀገር ውስጥ ፍጀታ የተረፈ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ለዚሁ ይረዳ ዘንድ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ በበኩላቸው ÷ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የጥራት ጉዳይ ለድርድር መቅረብ እንደሌለበትና ላኪዎችም ይህንን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።

ላኪዎችም በፊት ኢትዮጵያ የነበራት ገጽታ ተቀይሮ ከስንዴ አስመጪነት ወደ ላኪነት መሸጋገሯ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተጣለባቸውን ሀገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑ መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version