የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ-ካናዳ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በቶሮንቶ እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

November 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አራተኛው የኢትዮ-ካናዳ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በካናዳ ቶሮንቶ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በፎረሙ ላይ በካናዳ የኢትዮፕያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ እና የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ ታሳታፊዎች ናቸው።

የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት ይበልጥ በሚጠናከርበት አግባብ እና ኢትዮጵያ ያሏትን እድሎች ለማስተዋወቅ መቻሉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቀዋል፡፡

መድረኩም ለሀገራችን የወጪ ንግድ መዳረሻ በማስፋፋት ረገድ ምትክ የለሽና ወሳኝ ነው ብለዋል::

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!