የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

November 07, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ለመፈለግ እና አፍሪካን ጽኑ ለማድረግ በአብሮነት መሥራታችንን እንቀጥላለንም ብለዋል።