የሀገር ውስጥ ዜና

የአርቲስት አሊ ቢራ የክብር ሽኝት ነገ ይካሄዳል

By Meseret Awoke

November 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወዳጅነት አደባባይ በነገው ዕለት የአርቲስት አሊ ቢራ የክብር የአሸኛኘት ሥነስርዓት ይካሄዳል።

የቀብር አሰፈጻሚው ኮሚቴ ፥ አስክሬኑ ቢሾፍቱ ከሚገኘዉ የአርቲስት አሊ ቢራ መኖሪያ ቤት ወደ ወዳጅነት አደባባይ እንደሚመጣ ገልጿል፡፡

በወዳጅነት አደባባይ የክብር እና የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላ ወደ ድሬዳዋ አስክሬኑ እንደሚሸኝም ነው የተነገረው።

በድሬዳዋ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ከተካሄደ በኋላም የቀብር ሥነስርዓቱ እንደሚፈጸም ከወጣው መርሐ ግብር ማወቅ ተችሏል፡፡

በአዳነች አበበ