የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርቲስት ዓሊ ቢራ ህልፈት የተሠማቸውን ሀዘን ገለፁ

By Mekoya Hailemariam

November 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርቲስት ዓሊ ቢራ ህልፈት የተሠማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባወጡት የሀዘን መግለጫ የአንጋፋው ድምጻዊ ዓሊ ቢራ ኅልፈት ለኢትዮጵያ ጉዳት ነው ብለዋል።

“በዜማዎቹ ኅብረትን፣ ጽናትንና ባህልን አቀንቅኗል፤ ለብዙዎችም አርአያ ሆኗል። ላደረግከው ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግንሃለች።” ነው ያሉት።

አርቲስት ዓሊ ቢራ በሰባት ቋንቋዎች በማቀንቀን ለሰብዓዊ መብትና ለጭቁን ህዝቦች ድምፅ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የህዝብና የዓለም ሀብት ነው ብለዋል።

ሙዚቃዎቹ ዘመንን በመሻገር የሚደመጡ እና ለነገ ስንቅ የሚሆኑም እንደሆነ አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ለዘመዶቹ፣ ለወዳጆቹ እና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ተመኝተዋል።