የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአርትስት ዓሊ ቢራ ህልፈት የተሠማቸውን ሀዘን ገለፁ

By Mekoya Hailemariam

November 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአርትስት ዓሊ ቢራ ህልፈት የተሠማቸውን ሀዘን ገለፁ።

አቶ ሽመልስ ባወጡት የሀዘን መግለጫ፥ አርቲስት ዓሊ ቢራን “ባለ ድምፀ መረዋ፣ ሁለገብ የኦሮሞ ሙዚቃ መሠረት” ብለውታል።

አርቲስት ዓሊ ቢራን ማጣት መሪር ሀዘንን ፈጥሮብናል ብለዋል።

በዚህች ምድር ላይ ተወልዶ መኖር፣ ኖሮ ማለፍ የተፈጥሮ ህግጋት ቢሆንም፥ ለሰው ልጅች ትልቅ ታሪክንና ዕሴትን የፈጠሩ ሰዎች ህልፈትን ግን አምኖ መቀበል ከባድ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ኖሮ ማለፍ ላይቀር እንደ ዓሊ ቢራ የክብር ካባ ለብሰው ለሰው ልጆች ደስታ ሰርተው ያለፉ ግን ጥቂት ናቸው ብለዋል።

በክብር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን በእርሳቸው እና በክልሉ መንግስት ስም ገልፀዋል።

አቶ ሽመልስ ለኦሮም ህዝብ ብሎም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።