አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ገደብ አሳሳ የስንዴ ምርት አሰባሰብ ሂደትን ጎብኝቷል።
በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ በ987 ሔክታር ላይ በክላስተር የለማ የስንዴ ምርት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ታጭዶ እየተሰበሰበ ይገኛል።
ልዑኩ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሚኒስትሮችን እና የዲፕሎማቲክ አባላትን ያካተተ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!