አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በመንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን ትክክለኛ ስምምነት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ÷ ስምምነቱ የተፈረመው ከበርካታ እልህ አስጨራሽ የቡድን ክርክሮች እና ንግግሮች በኋላ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።
በመሆኑም ከሁለቱ ተወያይ ወገኖች የቀረቡ በርካታ ረቂቆች የነበሩ ቢሆንም ስምምነት ላይ የተደረሰበት እና ተቀባይነት አግኝቶ የተፈራረምንበት ሠነድ ግን ከዚህ በታች የተቀመጠው ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
አምባሳደር ሬድዋን እየተሰራጩ ያሉት መረጃዎች ቀደም ብለው የተዘጋጁ መረጃዎች ሊሆኑ እንደሚችሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።