ስፓርት

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በድሬዳዋ ይጀመራል

By Feven Bishaw

November 04, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጀመራል።

በቀጣዮቹ 5 ሳምንታት በድሬዳዋ የሚካሄዱት ጨዋታዎች የሰዓት ማሻሻያ የተደረገባቸው ሲሆን÷ጨዋታዎቹ 10 ሰዓት እና ምሽት 1 ሰዓት የሚካሄዱ ይሆናል።

በመርሐ ግብሩ መሰረትም ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከባህርዳር ከተማ እንዲሁም ምሽት 1 ሰዓት ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡