አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ42 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት አመራሮች የሣይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
ጎብኝዎቹ የሣይንስ ሙዚየሙን ከጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት በተመለከቱት ነገር መደነቃቸውን ገልጸዋል፡፡
ሙዚየሙ እና በውስጡ የተመለከቷቸው ነገሮች ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ ኩራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ በቴክኖሎጂ አብዮት ዋዜማ ላይ መሆኗን ኢትዮጵያ አንድ ማሳያ ናት ማለታቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የኢጋድ አመራሮችና ለጋሽ ተቋማት የሣይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
ከሌሎች የሥራ ዘርፎች በተጨማሪ በጤናው መስክም ተስፋ ሰጭ የቴክኖሎጅ ውጤቶች መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!