አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል ታስቧል፡፡
መታሰቢያው የተዘከረው በደም ልገሳ፣ ገንዘብ በማሰባሰብ እና የሠራዊቱን ጽናት በሚያሳዩ ዝግጅቶች ነው።
በርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ግቢ ጧፍ የማብራት ሥነ ስርዓትም ተከናውኗል፡፡
የክልሉ ሕዝብ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመታሰቢያው ላይ ተገልጿል፡፡
በመቅደስ አስፋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!