የሀገር ውስጥ ዜና

ከኅዳሴ ግድብ የሚመረተው ኃይል ወደ ዋናው ግሪድ እንዲገባ የሚካሄደው የመስመር ጥገና እና ፍተሻ ሥራ በቀጣይ ሣምንት ይጀመራል

By Alemayehu Geremew

November 02, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኅዳሴ ግድብ የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ዋናው ግሪድ እንዲገባ የሚካሄደው የመስመር ጥገና እና ፍተሻ ሥራ በሚቀጥለው ሣምንት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚገኙ ከ30 በላይ ወረዳዎችን አቆራርጦ አዲስ አበባ እንደሚገባም ነው የተገለጸው።

በዚህ ርቀት ውስጥ በሚሰሩ ሥራዎች የክልሎቹ የጸጥታ ኃይሎች እና መላው ነዋሪ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጠይቋል።

በሌላ በኩል የኢትዮ ኬንያ የኤሌክትሪክ የኃይል ሽያጭን ለማከናወን ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናቶች የኃይል ሽያጩ ይጀመራል ተብሏል።

በመጀመሪያው ሽያጭም 200 ሜጋ ዋት ኃይል ይቀርባል ነው የተባለው።

የኃይል ግዢ ስምምነቱ ባለፈው ነሐሴ ወር መፈረሙ የሚታወስ ነው።

በቆንጅት ዘውዴ