የሀገር ውስጥ ዜና

በሩብ ዓመቱ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

By Tamrat Bishaw

November 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዙን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የፌደራል ፖሊስ፣ገቢዎች ሚኒስቴር እና ፍትህ ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የኮንትሮባንድ መከላከል ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገሙ ነው።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ተገኔ ደረሰ እንዳሉት÷ የኮንትሮባንድ ወጪና ገቢ ዕቃዎችን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ግምታዊ ዋጋቸው 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የሚሆኑ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች እንደተያዙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘገቧል፡፡

በኮንትሮባንድ ተግባር የተሳተፉ 351 ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ነው ዳይሬክተሩ ያነሱት።