Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጤና ሚኒስቴር “ኢላንጋ” ከተሰኘ የስዊዘርላንድ የበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር “ኢላንጋ” ከተሰኘ የስዊዘርላንድ የበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ሥምምነቱ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና አገልግሎቶች በሕክምና ቁሳቁስ ለመደገፍና ወደ ሥራ ለማስገባት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

“ኢላንጋ” የተሰኘው የስዊዘርላንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ÷ በጦርነቶች እና ግጭቶች የወደሙ የጤና ተቋማትን በሚያስፈልጋቸው የሕክምና ቁሳቁስ በመደገፍ ወደ አገልግሎት ለማስገባት እና የሰው ልጆችን ተሥፋ ለመመለስ የሚሰራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለኢላንጋ ፕሬዚዳንት አን ማሪ ጌርትስ እና የበጎ አድራጎት ቡድናቸው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version