ኮሮናቫይረስ

ሳሙና ፣ ሳኒታይዘሮች እና ሙቅ ውሃ ከኮሮናናሌሎች ቫይረሶችን ለመከላከል ምን ያህል ይረዱናል?

By Meseret Demissu

March 24, 2020

አዲስ አበባ፣መጋቢት 15፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል እጅን በሳሙና ፣ በሳኒታይዘሮች እና በሙቅ ውሃ ደጋግሞ መታጠብ አንዱ የመከላከያ እርምጃ ነው፡፡

እነዚህ የእጅ የንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶች ቫይረሱን በመከላከል ረገድ እንዴት እና ምን ያህል ይረዳሉናል? የኮረና ቫይረስ በአጉሊ መነጽር ሲታይ ባለ ጠቋሚ ነጠብጣቦች ተሸፍነው ይታያሉ ፣ እናም ይህ በራሳቸው ላይ ዘውድ ወይም ኮሮና እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል።

ዘውድ ብለን የምንጠራው የቫይረሱ ውጫዊ ክፍል ሲሆን ከቅባትማ ወይም ስብ የተሰራ ነው ።

አሁን ኮሮናቫይረስ በቅቤ የተሸፈነ የቅቤ ምግብ እንደሆነ ያስቡ ፡፡ የተመገቡበትን እቃ በውሃ ብቻ ለማጠብ ቢሞክሩ ያ ቅቤ ከእቃው ላይ አይለቅም ቅባቱን ለማስለቀቅ ጥቂት ሳሙና ያስፈልጋል፡፡

ስለሆነም በተመሳሳይ ሁኔታ የኮሮና ቫይረስን በቅባትነት የሸፈነውን ቅባትማ ነገር በሳሙና ወይም አልኮሆል የሆነ የንጽህና መጠበቂያ በመጠቀም የቫይረሱ ፈሳሽ ሽፋን እንዳይሰራጭ በማድረግ በኩል በጣም ውጤታማ ናቸው፡፡

ቫይረሱ ወይም ባክቴሪያ አንዴ ከተከፈተ ወይም የውጭውን ክፍል ካጣ በሳሙናና ውሃ ውስጥ በመፍሰስ ይሞታል ፡፡ ስለሆነም በሚታጠቡበት ወቅት እጆችዎን በውሃና በሳሙና ጣትዎችን ጨምሮ ለ20 ሰከንዶች ያህል በማሸትና በመቧጠጥ መታጠብ ያስፈልጋል።

ይህ ደግሞ በእጅዎ ላይ የቀሩትን የባክቴሪያ ፣ ቫይረሶች እና ሌሎች ጀርሞች ቅሪተ አካል ለማስወገድ የሚያስችላቸውን ኬሚካላዊ ትስስር በመፍጠር እጅዎን ንጹህ ያደረጋል።

ብዙውን ጊዜ የሚታጠቡበት ውሃ ሞቅ ያለ ቢሆን ይመረጣል÷ የሙቀት መጠኑም የቫይረሱን ወይም የባክቴሪያውን የውጭኛው ክፍል ቆዳ መላጥ የሚያስችል መሆን ይኖርበታል።

ከዚያም ባለፈ የሞቀ ውሃ ሳሙናው የተሻለ አረፋ እንዲኖረው በማድረግ ÷ሳሙናው በበለጠ ሁኔታ ቆሻሻና ባክቴሪያዎችን እንዲሁም በውስጣቸው ያሉትን ቫይረሶች እንዲገድል ያደርጋቸዋል ተብሏል።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሳሙናና ከሞቀ ውሃ በተጨማሪ÷ በአልኮል ላይ የተመሰረቱ የእጅ ማፅጃዎች በትክክል ጥቅም ላይ ከዋሉ የሳሙናን ያህል ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል።

ነገር ግን እነዚህ የአልኮል ማጽጃዎች ቢያንስ 60% የአልኮል ባህሪያት በውስጣቸው ሊኖራቸው ይገባል ነው የተባለው።

ከዚያም ባለፈ ትንሽ ጠብታ በእጅዎ መዳፍ ላይ ማድረጉ እና በፍጥነት ማጽዳት ብቻ ቫይረሱን ለማስወገድ በቂ አይደለም።

ስለሆነም ተፈላጊውን ውጤት ለማግኘት የአልኮል ማጽጃዎቹን በእጅ መዳፍ ውስጥ ጠብ በማድረግ ጣትዎች ጨምሮ ሁሉንም የእጅ ክፍሎች ማሸት አስፈላጊ ነው።

 

 

ምንጭ፡-ሲ.ኤን.ኤን