Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አዲሱ የመጅሊስ አመራር ልዑክ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ አዲሱ የመጅሊስ አመራር ልዑክ ዛሬ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ትውውቅ አድርጓል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሕዝበ ሙስሊሙ አንድነት ለሀገራችን ዘላቂ ሠላምና ልማት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል፡፡
አስተዳደሩ ከአዲሱ አመራር ጋር በሁሉም ዘርፍ ተቀራርቦ ለመሥራት ዝግጁ ነው ማለታቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
አዲሱ የመጅሊስ አመራሮች በድሬዳዋ ሕዝብና አስተዳደር ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version