በአዲስ አበባ በሚካሄደው አህጉር አቀፍ የወጣቶች ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ እንግዶች እየገቡ ነው

By Tamrat Bishaw

October 28, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለእንግዶቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች እና ሚኒስትሮች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የተለያዩ የአፍሪካ ገገራት ልዑካን ፣ ወጣቶች እና የቀድሞ ፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ቤተሰቦች በጉባኤው ላይ ለመታደም ነው ውደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉት።

ጉባኤው ለሶስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የአፍሪካ ወጣቶች በፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ ተጽዕኖ ፈጣሪ አፍሪካን መፍጠር ትኩረት ያደረገ ነው።

ጉባኤው የተዘጋጀው ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተበባር መሆኑ ተገልጿል።

በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት እንዴት ጠንካራ አፍሪካን እንፍጠር ፣ ከወጣቶች ምን ይጠበቃል? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል ።

በመድረኩ የአህጉሪቱ የቀድሞ መሪዎች ለአፍሪካ አንድነት መጠናከር እንዲሁም ለፓን አፍሪካኒዝም ማበብ ያበረከቱት አስተዋጽኦ የሚወሳ ይሆናል ።

በጉባኤው ማጠቃለያ ላይም ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መጠናከር ሚና ለነበራቸው መሪዎች ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።