የሀገር ውስጥ ዜና

የግሉ ዘርፍ የጤና ተቋማት የቤተሰብ ዕቅድ አሰጣጥን የሚመለከት ጥናት ይፋ ሆነ

By ዮሐንስ ደርበው

October 28, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግሉ ዘርፍ የጤና ተቋማት የቤተሰብ ዕቅድ አሰጣጥን የሚመለከት ጥናት ይፋ ተደረገ።

ጥናቱ በሃንዝ አማካሪ የተሰራ ሲሆን፥ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ደግሞ ጥናቱ እንዲደረግ ድጋፍ አድርጓል።

በጥናቱ መሰረት 12 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች በግሉ ዘርፍ የጤና ተቋማት የቤተሰብ ዕቅድ ክትትል እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ጥናቱ ከትግራይ እና አፋር ክልሎች ውጪ በሁሉም ክልሎች የተደረገ ሲሆን ለጤና ሚኒስቴርና መሰል ተቋማት ትልቅ ግብአት ይሆናል ተብሏል።

በዘመን በየነ