Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶክተር ይልቃል ከፋለ ታይም ጅብሰም ፋብሪካን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በደጀን ከተማ የተገነባውን የታይም ጅብሰም ፋብሪካን መርቀው ሥራ አስጀመሩ፡፡
በ1 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፋብሪካው÷ በቀን 500 ቶን ጅብሰም የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡
ዶክተር ይልቃል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በተለይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን አጠናቆ ወደስራ የገባ ፕሮጀክት በመሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡
ምርት ወደ ማምረት የተሸጋገሩና በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በቅርበት በመደገፍ ዘረፉ ይበልጥ እንዲያብብ እንሠራለን ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version