Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዓለም በከፍተኛ የሃይል ቀውስ ውስጥ ገብታለች – ዓለም አቀፉ የሃይል ኤጀንሲ

Dr. Fatih Birol, Executive Director of the International Energy Agency speaks during the 15th Singapore International Energy Week, in Singapore October 25, 2022. REUTERS/Isabel Kua

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም በከፍተኛ የሃይል ቀውስ ውስጥ መግባቷን ዓለም አቀፉ የሃይል ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ኃላፊ ፌዝ ቢሮል በሲንጋፖር በተካሄደው ዓለም አቀፉ የኃይል ሣምንት ተገኝተው፥ ዓለም ስለገጠማት የሃይል እጥረትና መፍትሄዎቹ አብራርተዋል፡፡

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈሳሸ የተፈጥሮ ጋዝ ገበያ ስለተፈጠረው ችግርና ዋና ዋና የነዳጅ አምራቾች አቅርቦትን መቀነስ ዓለማችን በኃይል እጥረት ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል ነው ያሉት፡፡

ወደ አውሮፓ የሚገባው የተፈጥሮ ጋዝና ቻይና የነዳጁ ፍላጎቷ እየጨመረ መምጣቱ በሚቀጥለው ዓመት ለግብይት የሚቀርበው 20 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር አዲስ የተፈጥሮ ጋዝ ብቻ በመሆኑ ገበያው ላይ ሌላ ውጥረት እንደሚመጣ ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም፥ የነዳጅ ላኪ ሀገራት (ኦፔክ) እና አጋሮቹ በቅርቡ በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰኑት ውሳኔንም ኮንነዋል፡፡

በዚህ ዓመት የዓለም የነዳጅ ፍላጎት በቀን ወደ 2 ሚሊየን በርሜል የሚጠጋ ዕድገት ማሳየቱንም ነው የገለጹት፡፡

ለነዳጅ ዘይት ፍጆታ በ2023 በቀን በቀን በ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን በርሜል ጭማሪ ይኖረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት ኃላፊው ፥ ዓለም የነዳጅ ፍላጎቷን ለማሟላት የሩሲያ ነዳጅን ትሻለች ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ዓለም ያጋጠማት የኃይል ቀውስ ዘላቂና ደህንነቱ የተጠበቀ የኃይል ስርዓት እንዲኖራት የሚያስችል አጋጣሚ ሊሆን ይችላል ሲሉም ነው የተናጉት፡፡

ይህን ችግር ተከትሎም የዓለም ሀገራት የኃይል ቴክኖሎጂዎችንና ታዳሽ ኃይሎችን መጠቀም መጀመርና የነዳጅ ኃይልን እንደብቸኛ የሃይል ምንጭ ባለመጠቀም ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት እንደሚችሉም ነው ያነሱት፡፡

የተለያዩ ሀገራትም ከነዳጅ እጥረት ቀውሱ ለመውጣት የታዳሽ ኃይልን በመጠቀም የኃይል ፍላጎታቸውን ለማሟላት እየሞከሩ እንደሆነ መግለጻቸውን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው፡፡

Exit mobile version