አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓመቱ ለሁለተኛ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚታየው የፀሐይ ግርዶሽ በመላው ዓለም ተከስቷል፡፡
በዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ÷ ጨረቃ በፀሐይ እና በመሬት መካከል የምታልፍ በመሆኗ የተከሰተ ነው፡፡
ክስተቱ አብዛኛውን የፀሐይ ብርሃን የከለለ ሲሆን ጥላው ደግሞ ምድራችን ላይ አርፏል፡፡
በውጤቱም ከፊል ጨረቃ መሠል ቅርፅ የያዘ አይን የሚያጥበረብር ብርሃን በሰማይ ላይ መታየቱን ዴይሊ ቻይና ዘግቧል፡፡
ዛሬ የተከሰተው ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ÷ በግሪን ላንድ ፣ አይስላንድ ፣ በአብዛኛው የአውሮፓ ክፍል ፣ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ ፣ በምዕራብ እና መካከለኛው እስያ ታይቷል ነው የተባለው፡፡
በአብዛኛው የሰሜን ንፍቀ ክበብ የተከሰተው ይህ ከፊል የፀሐይ ግርዶሹ በኢትዮጵያ ሠዓት አቆጣጠር ከአመሻሽ 11 ሠዓት ከ 30 ጀምሮ መታየቱ ነው የተገለፀው፡፡