Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመከላከያ ሰራዊት ቀን በፓሽን አካዳሚ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት ቀን “ስለተሰዋልን ደም እና አጥንት ስለተከፈለልን ህይወት፣ ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በፓሽን አካዳሚ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ የአካዳሚው ሰራተኞች፣ተማሪዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በመርሐ ግብሩ ላይ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዲፈራ የሀገር ሰላም ወሳኝ እና ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለዚህ ደግሞ መከላከያ ሰራዊት እየከፈለ ላለው የህይወት ተጋድሎ ክብር መስጠት ያስፈልጋል ነው የተባለው።

የመከላከያ ሰራዊት ቀን “ህዝባችን የጥንካሬያችን ምንጭ ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ቀን እንደሚከበር መገለፁ ይታወሳል።

 

 

Exit mobile version