የሀገር ውስጥ ዜና

ትኩረቱን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያደረገ ስብሰባ በጂቡቲ እየተካሄደ ነው

By Tamrat Bishaw

October 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት ትኩረቱን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያደረገ ስብሰባ በጂቡቲ እየተካሄደ ነው፡፡

ስብሰባው የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በይፋ አስጀምረዋል፡፡

በሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም የተመራ ልዑክ በስብሰባው እየተሳተፈ ነው፡፡

ስብሰባው “የአየር ንብረት ለውጥ እና ምርምር እንዲሁም ለዘላቂ መላመድ እና የመቋቋም መንገድ” በሚል ርዕስ እየተካሄደ መሆኑን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያላክታል፡፡