አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚደግፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
በተሁለደሬ፣ ሀይቅ፣ ቃሉ፣ ከለላ፣ ወረባቦ፣ ተንታ፣ ሀርቡ፣ በወልዲያ፣ ከሚሴ፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደብረ ታቦር፣ መካነ ኢየሱስ፣ ወረታ፣ ደብረ ማርቆስ፣ እንጅባራ፣ ላይ አርማጭሆ ወረዳ፣ ትክል ድንጋይ፣ወገራ ከተማ እና ገንዳ ውሃ÷ “ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ፤ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ሐሳብ የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት እና አሸባሪው ህወሓትን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
የሰልፉ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት÷ አሸባሪው ህወሓት ወደ ሰላም በመምጣት ወጣቶችን ከማስጨረስ እንዲታቀብ ጠይቀዋል፡፡
የሀገርን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ የውጭ ጣልቃ ገቦችም ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የትግራይ ሕዝብና የኢትዮጵያ ሕዝብ አይነጣጠሉም ጠላታችን አሸባሪው ህወሓት ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡
የሀይቅ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክፍሉ አማረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በሀገር ሉዓላዊነት ለሚደረግ ጣልቃ ገብነት የዛሬው ሰልፍ መልስ የሰጠ ነው፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!