Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለጉብኝት ጅማ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጉብኝት ጅማ ከተማ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጅማ የገቡት ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከተለያዩ ሚኒስትሮች ጋር በመሆን ነው።

ልዑኩ ጅማ ሲደርስም በመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና በሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በአልዓዛር ታደለ

Exit mobile version