Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየርሊጉ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቀን 7 ሰዓት  በባህርዳር አለማቀፍ ስታዲየም ጨዋታውንያደረገው መቻል በእስራኤል እሸቱ ብቸኛ ጎል ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

10 ሰዓት ላይ በተከናወነ ሌላ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ወላይታ ዲቻን በተመሳሳይ 1 ለ 0 መርታት ችሏል፡፡

ሲሞን ፒተር ደግሞ ብቸኛዋን የመድን ጎል ያሰቆጠረ ተጫዋች ነው፡፡

ኢትዮጵያ መድን በቅዱስ ጊዮርጊስ ከደረሰበት የ 7 ለ 1 ሽንፈት በማገገም በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል፡፡

Exit mobile version