የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከተመድ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ ከፍተኛ ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

By Tamrat Bishaw

October 21, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ቢሮ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ጋር ውይይት አደረጉ።

አምባሳደር ዘነበ ከኮሚሽነር ተርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሁለቱ አካላት ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በተመድ የስደተኞች አገልግሎት ረዳት ከፍተኛ ኮሚሽነር በመሆን ያገለገሉት ኦስትሪያዊ የሕግ ባለሙያ ቮልከር ተርክ በሚሼል ባቺሌት ቦታ መተካታቸው ይታወቃል።