አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታል መስራች ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።
የዶክተር ካትሪን ሐምሊን አስከሬን የሽኝት ፕሮግራም በመኖሪያ ቤታቸው ከተደረገ በኋላ የቀብር ስነ ስርዓታቸው በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል።
በስነ ስርዓቱ ላይም የዶክተር ካትሪን ሐምሊን ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል።
ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።
ዶክተር ካትሪን ሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በማቋቋም ከ60 ዓመታት በላይ የፌስቱላ ህክምናን ሰጥተዋል።
በበጎ ተግባር ላይ ተሰማርተው የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ችግርን የቀረፉት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።
በሳራ መኮንን
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision