የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

October 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ፡፡

ምክር ቤቱ በስብሰባው÷ ከ1ኛ መደበኛ ስብሰባ የተሸጋገሩ ሦስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

በተጨማሪም የቋሚ ኮሚቴዎችን አደረጃጀት ለማሻሻል የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!