የሀገር ውስጥ ዜና

የአዋሽ መልካሳ የኬሚካል ፋብሪካን የማምረት አቅም ለማሳደግ እንሰራለን – ኢ/ር ታከለ ዑማ

By Meseret Awoke

October 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዋሽ መልካሳ የኬሚካል ፋብሪካ ያሉበትን ችግሮች በመፍታት የማምረት አቅሙን ለማሳደግ እንሰራለን ሲሉ የማዕድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ዑማ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ለሀገራት ኢንደስትሪ እድገት መሰረት የሆነውን የሰልፈሪክ አሲድን በሚያመርተው የአዋሽ መልካሳ የኬሚካል ፉብሪካ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፋብሪካው በተለይም ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ለማምረት እንደ ግብአት ልናውለው የምንችለውን ሰልፈሪክ አሲድና ለውሀ ማጣሪያ የሚውለውን አልሙኒየም ሰልፌት በዋነኝነት እያመረተ ይገኛልም ነው ያሉት።

ሆኖም ፋብሪካው ባለበት የግብአት ችግር ምክንያት ማምረት በሚችለው ልክ እያመረተ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

ምርቱም በግብርናውና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚኖረው ሚና ሲታይ የፋብሪካውን መደገፍ ትልቁ አማራጭ እንደሚሆንም ነው የጠቆሙት፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ፥ በቀጣይም ፋብሪካው ያሉበት ችግሮች ተፈተው የማምረት አቅሙን እንዲያሳድግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!