የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ ሀገራት ከተሞች ሃላፊዎች ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

October 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚላን የከተማ ምግብ ፖሊሲ ስምምነት ግሎባል ፎረም ቆይታቸው ከተለያዩ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባዋ በቆይታቸው ከሪዮ ዴጄኔሮ ከንቲባ ኤድዋርዶ ዳኮስታ ፣ ከሚላን ከተማ ምክትል ከንቲባና የሚላን የምግብ ተስማሚነት ፖሊሲ ሃላፊ ከሆኑት አና ስካቩዞ እንዲሁም ከፓሪስ ከተማ ምክትል ከንቲባ ከሆኑት ኦድሬ ፑልቫር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በከተሞቹም መካከል የሁለትዮሽ ጠንካራ ግንኙነት የመመስረትና ቀጣይ ትብብርን የሚያጠናክሩ አለፍ ሲልም የእህትማማች ከተማነት ግንኙነትን ለመጀመር የሚያስችሉ ምክክሮች እንደሆኑም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!