የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ በሸቤለይ ወረዳ ዘመናዊ የግመል ማራቢያ ማዕከልን ጎበኙ

By Feven Bishaw

October 18, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ሸቤለይ ወረዳ ዘመናዊ የግመል ማራቢያ ማዕከልን ከልዑካቸው ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ እና ልዑካቸው በትናንትናው ዕለት ከርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

እንዲሁም ልዑካኑ በጅግጅጋ ከተማ በፌዴራል እና በክልሉ መንግሥት የተሰሩ እንዲሁም በመገንባት ላይ የሚገኙ በርካታ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውም የሚታወስ ነው፡፡