Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ድርድር ላለማድረግ የያዘችውን አቋም እንደማትለውጥ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከአሜሪካ ጋር ድርድር ላለማድረግ የያዝነውን አቋም አንለውጥም አሉ የኢራን ሀይማኖታዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ።

ቴህራን ለዋሽንግተን ግፊት እጅ እንደማትሰጥም ነው አያቶላህ አሊ ሃሚኒ የገለጹት።

ሀይማኖታዊ መሪው ከጠላት ጋር የሚደረግ ድርድር ችግራችንን ይፈታል ብሎ የሚያምን አካል መቶ በመቶ ተሳስቷልም ብለዋል።

አሜሪካ የኢራን የመጨረሻውን ንጉስ ሞሃመድ ሬዛ ሻህ ትረዳለች በሚል የምትወቅሰው ኢራን፤ በ1979ቱ አቢዮት በቴህራን የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ተቆጣጥራ ነበር።

በወቅቱ 52 አሜሪካውያንን በኤምባሲው ለ444 ቀናት እንዲቆዩ ማድረጓም የሚታወስ ነው።

ይህንኑ ቀን በልዩ ሁኔታ ለመዘከር በየአመቱ በምታሰናዳው በዓልም ኢራናውያን “ሞት ለአሜሪካ” የሚል መፈክር ይዘው አደባባይ እንደሚወጡ ነው የተገለፀው

የዚህ በዓል 40ኛ አመት ነገ ሲከበርም የተካረረውን የቴህራን እና ዋሽንግተን ፍጥጫ ይበልጥ እንዳያንረው ተሰግቷል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

Exit mobile version